ከፌደራል እስከ ቀበሌ መዋቅር ድረስ ላላችሁ ለወላይታ አመራሮች

Wolaita Today

ከ “Aydamiyaa” የወላይታ ሴቶች የቀረበ የአጋርነት ጥሪ

August 10, 2020

መንግስት ኢ-ፍትሃዊ በሆነ መንገድ የወላይታ አለኝታ በመሆን ትግሉን ሲመሩ የነበሩ የፊት አመራሮችን፡ የላጋዎችን፡ምሁራንን፡ የተፎካካሪ ፖለቲካ ፓርቲ መሪዎችንና ሌሎች ሰላማዊ ግለሰቦችን ከአባቶቻችን ጉታራ በማፈን መውሰዱ ይታወቃል።

ይህም አልበቃ ብሎት የመንግስት ድንገተኛ ወረራና የሰላማዊ ልጆቹ መታፈን አስደንግጦት ለሰላማዊ ተቋውሞ እጁን አጣምሮ ቢወጣ ግብር ከፍሎ ለዳር ድንበር ለጠላት ባሰናዳው መከታዬ በሚለው የመከላከያ ሰራዊት በተከፈተበት የጥይት እሩምታ ንጹህ ነፍሶችን ገብሮ እንደለመደው እዝን ተቀምጧል።

ስለሆነም ነገ የናነተ እጣ ፈንታም ስላልተለየ ለራሳችሁም ለወከላችሁም ህዝብ ስትሉ ያለጥፋታቸው የህዝብን ጥያቄ ስላስተጋቡ ብቻ የሚንገላቱ ጓዶቻችሁን ፈለግ ተከትላችሁ “ያለነሱ አንሰራም” በማለት ህዝባዊ ትግሉን ትቅላቀሉና ትመሩ ዘንድ አበክረን እንጠይቃለን።
ከዛ እስቲ IMPORT በተደረገ አመራር ያስመራን እንደሆነ እናያለን።

ያንን ማድረግ ባትችሉ ከወራሪዎቻችን ለይተን ስለማናያችሁ ትግላችን በግልጽ ከናንተ ጋርም እንደሚሆን መግለጽ እንወዳለን።

SHAKKIDI DAANAA